አዲስ ማለዳ
በግል ባለቤትነት ስር ያለ ጋዜጣ ነው። · 33.6K
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች
- የምዕራብ ሳሃራ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ መጠናቀቁን ተከትሎ ተመድ የጸጥታ ስጋት እንዳለ አስጠነቀቀ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮውን የሥራ ዘመን ለማራዘም ባለመቻሉ በምዕራብ ሳሃራ ሊከሰት የሚችለውን የጸጥታ ስጋት አስጠነቀቀ። የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ እስቴፈን ዱጃሪክ የቀጣናው ሀገራት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያሳዩ እና ሰላም ሊያደፈርሱ ከሚችሉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
- እስካሁን የ24 ተፈናቃዮች አስክሬን አንስተናል - የአይን እማኞች
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ "ቱርክ ካምፕ" በተባለው የተፈናቃዮች መጠለያ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 24 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ30 በላይ መቁሰላቸውን በስፍራው ያሉ ተፈናቃዮች ለቦርከና ተናግረዋል። የአይን እማኞቹ የጉዳቱ መጠን ሊጨምር እንደሚችል ገልጸዋል።